በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በባቢሌ ወረዳ በኤረር

ኢባዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበርኢባዳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ 6 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ለሁለት ቀን ያደረውን ዝሆን ህይወት መታደግ መቻሉን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የዝሆኖች ምርምር አስተባባሪ አቶ አንተነህ በላይነህ ገለጹ፡፡

አቶ አንተነህ ጥር 20/2007 ዓ.ም እንደ ገለጹት ዝሆኑ ውሃ ጠጥቶ ሲወጣ ከሰውነቱ ግዙፍነት የተነሣ ወደ ኋላው ሲዞር ተንሸራቶ 6 ሜትር ጥልቀት ባለው የውሃ ጉድጓድ ገብቶ የተገኘ ሲሆን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የዝሆኖች ምርምር ቡድን አባለት ከዝሆኖች ምርምር ጋር ለተያያዘ ስራ ወደ ስፍራው ሲሄዱ ግመል የሚጠብቁ አርብቶ አደሮች ጥቆማውን ያደርሳሉ፡፡

The Haramaya University Wildlife Research Team supported the life of an elephant, elephant image

ተማራማሪዎቹም የሄዱበትን ስራ በመተው የዝሆኑን ህይወት ለመታደግ የአካበቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር በመጀመርያ ደረጃ እዚያው ጓድጓድ ወስጥ ዝሆኑ አየር አንዲያገኝ እና ከዝሆን ተፈጥሮ አንጻር ፋንድያውን ቶሎ ቶሎ ካልጣለ ሊሞት ስለሚችል 24 ሰዓት የፈጀ ቁፍሮ ከተካሔደ በኋላ ለፈንደያው መጠያ ሌላ ቀዳዳ በመስራት ሆዱ ተነፋፍቶ የነበረውን ዝሆን ፋንድያውን አንዲጥል ተደርጓል ፡፡

በሁለተኛው ቀን ዝሆኑ እዚያው ባለበት ምግብ ኢንዲሰጠው ተደርጎ ካደረ በኋላ እንስሳውን ለማወጣት ከፍተኛ ማሽን በማስፈለጉ በአካባቢው በውሃ ኮንስትራክሽን ስራ በተሰማራው ወርቁ ተፈራ የውሃ ስራዎች ድርጅት በተገኘ እስካቫተር እና በአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ርብርብ ስድስት ሜትር ገደል ተሠርቶለት ዝሆኑ በራሱ አንዲወጣ ከተደረገ ብኋላ ከመንጋው ጋር ተቀላቅሎ በአሁኑ ስዓት የተለመደ ኑሮውን እንዲጀምር መደረጉ ታውቋል፡፡

The Haramaya University Wildlife Research Team supported the life of an elephant, elephant image

The Haramaya University Wildlife Research Team supported the life of an elephant, elephant image

Elephant image

በመጨረሻም ይህን እጅግ ፈተኝ የሆነውን ከፍተኛ የሰው ኃይልና የማሽን ድጋፍ የሚጠይቅ በዝሆኑ የህይወት የማዳን ስራ ላይ የተባበሩንን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ም/ፕርዝዳንት ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳን፤የባቢሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ፤ ወርቁ ተፈራ የውሃ ስራዎች ድርጅትን፤የአካባቢው ማህበረሰብ አባላትን እንዲሁም የዝሆን ተመራማሪ የሆኑት አቶ ስንታየ ወርቅነህ እዚያው ጫካ ውስጥ ለሁለት ቀናት በማደር ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት እና ቡድኑን በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋፆ ላደረጉት አካላት በሙሉ አቶ አንተነህ አመስግነው ኅብረተሰቡ አንዲህ አይነት ጥልቅ የውሃ ጉጓዶችን በሚያዘጋጅበት ጊዜ የዝሆንም ሆነ የሌሎችን እንስሳት ህይወት አደጋ ወስጥ እንዳይከት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርቧል ሲል ሲሣይ ዋቄ ዘግቧል፡፡