ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለስድስት አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎቹ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዛሬ ሰጠ፡፡
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ገምግሞ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት
1. ለዶ/ር ማሽላ ደጀኔ ወልደሚካኤል በዕፅዋት በሽታ ጥናት “ፕላንት ፓቶሎጂ”፣
2. ለዶ/ር ዋሱ መሐመድ አሊ በዕፅዋት ዝርያ ማሻሻል “ፕላንት ብሪዲንግ” ፣
3. ለዶ/ር ንጉሴ ቡሳ ፌዳሳ በ”ባዮኬሚስትሪ እና ፊዚዮሎጂ” ፣
4. ለዶክተር አቢ ታደሰ በ”ኢንኦርጋኒክ ኬሚስትሪ” ፣
5. ለዶ/ር ምትኩ እሸቱ ጉያ በእንስሳት እርባታ ፣
6. ለዶ/ር ተስፋሕይወት ዘሪሁን በቨተርነሪ ክሊኒካል ፓቶሎጂ (ስነ ደዌ) የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡