የሐረሪ ክልል የሴቶች ፣ ህጻትና ወጣቶች ቢሮ በ2009 ዓ.ም በክልሉ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በሴቶችና ህጻናት መብት አጠባበቅ ላይ በስፋት ለመስራት እንዲያስችለው ለሶስት ቀናት ከክልሉ ከተለያዩ ቢሮዎች ለተውጣጡ አርባ አምስት ባለሞያዎች ስልጠና ሰጥቷል ፡፡
ስልጠናው በዋነኛነት በሴቶችና ህጻናት መብቶች ዙሪያ ዓለም አቀፍ ፣ አህጉራዊና አገራዊ የሆኑ ህጎች ድንጋጌዎች መሰረት የተሰጠ ሲሆን ከህጉ አንጻርም በተግባር ያሉ ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል ፡፡

የስልጠናው ተካፋይ ሲስተር ጸሀይ ወርቅአለማሁ በበኩላቸው እንደተናገሩት ስልጠናው አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ህጎች ለሴቶችና ህጻናት የሚሰጡትን መብትና የመንግስት አካላትም መብቶቹን ለማስከበር ያለባቸውን ሀላፊነት በተመለከተ ሰፊ ትምህርት እንዳገኙ ገልጸው ይህን መሰል ስልጠና አስፈጻሚ አካላት በትግበራ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ለሚሰሩት ስራ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ወደ ፊት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ተናግረዋል ፡፡