በሸምሸዲን መኸመድ ከህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

መጋቢት 19 ቀን 2007 ዓ.ም በድሬደዋ ስታዲዮም ላይ በተካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤን ቡድን ተጋጣሚውን የድሬደዋ ቀይ መስቀል የጤና ቡድንን 2 ለ 1 በማሸነፍ  ዋንጫ ባለቤት መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የውስጥና የውጪ ስፖርት ውድድሮች ደይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምመላሽ ተስፋዬ ለየሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ደይሬክቶሬት ዘጋቢ እንደገለፁት’የዚህ ስፖርታዊ ውድድር ዋና አላማው አሻናፊና ተሸናፊ ለመለየት ሳይሆን ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን ያለንን ፍቅር የለመግለጥና ህዝቡን ይበልጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ደምመላሽ እንደተናገሩት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ማህበረሰብ ለግድቡ ግንባታ ከቦንድ ግዢ አንስቶ በልዩ ልዩ ተግባራት ተሳትፎ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስረድተው ዳይሬክቶሬቱ ከሚሰራቸው ስራዎች በዋንኝነት የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ከቀለም ት/ት በተጨማሪ በስፖርት የዳበረ ጤናማ አካል እንዲኖራቸው እንዲሁም የእርስ በርስ ግንኙነታቸው እንዲዳብርና የተወዳዳሪነት መንፈሳቸው ለማገዝ ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም ለዚህም ግብ መሳካት የተማሪዎችን የውስጥ ለውስጥ በተለያዩ ስፖርት አይነቶች ውድድር በየዲፓርትመንቶችና በኮሌጆች መካከል በደመቀ ሁኔታ በማካሄድ ላይ መሁኑን ገልጸው ይህም ተግባር ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለመምህራንና ለሰራተኞች አስፈላጊ መሆኑን ስላመነበት በኮሌጆች መካከል የእግር ኳስ ውድድር እንዲጀመር ማድረጋቸውን አስረድተዋል ፡፡

በተመሳሳይ መልኩም በፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ .ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የታለቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት የተቀመጠበትን 4ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች ቡድንና በጊቢው ማህበረሰብ የጤና ቡድን መካከል የእግር ኳስ እንድሁም ሴት ተመራቂ ተማሪዎች ከ ሴት ተመራቂ ካልሆኑ ተማሪዎች መካከል የገመድ ጉተታ ውድድር እንደሚካሄድ አስረድተው መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ተማሪዎች በእለቱ በአሮጌው ስታድዮም በመገኘት ጫወታውን እንዲመለከት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡