የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ380 ሺህ ብር የገዛቸውን 200 ፍየሎችና በ77ሺ ብር የገዛውን መኖ በሐረማያ ወረዳ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሴት አርሶአደሮች አከፋፈለ፡፡

ቤነፊት ሪያላዝድ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ክላስተር እርዳታውን ያደረገው አነስተኛ ገቢ ላላቸው የኢዶ-በሊናና ሀቀ-ፈላና ሴት አርሶ አደሮችና በአንበጣ መንጋ ሰብላቸውን ለወደመባቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በድጋፉ ለእንያንዳንዳቸው ሴት አርሶ አደሮች አምስት ፍየሎችንና ለ3 ወር የሚበቃ የተመጣጠነ የፍየል መኖ ነው፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው የኢዶ በሊና ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ኢፍቱ የተመጣጠነ የፍየል መኖ ለመውሰድ እንደመጣች ተናገራለች። የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች አደራጅተውን ገቢያችንን ለማሳደግ የሚረዳ በቂ ስልጠና ከሰጡን በኋላ ለእያንዳንዳችን አምስት ፍየሎችን የሰጡን ሲሆን አንበጣ ሰብላችንን ባወደመበት በአሁኑ ሰዓት ለ3 ወር የሚበቃ ተጨማሪ የፍየል መኖ ሰጥተውናል ብለዋል፡፡

ወይዘሮ መፍቱሃ በበኩሏ አምስት ፍሎችና ለፍየሎቹ ለምግብነት የሚውል 1 ኩንታል ፉርሽካና ሁለት ጀሪካን ሞላሰስ ማግኘቷን ገልጻ በተለይ አንበጣ ሰብላችንን ባወደመበት ሰዓት ስለደረሰልን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲን እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

የቤነፊት ሪያላይዝድ የማህበራዊ ምጣኔ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጃፈር ሙሜ እንደገለፁት በሴፍቲኔት ለታቀፉ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 40 ሴት አርሶ አደሮች 200 ፍየሎችን ገዝተው አከፋፍለዋል።