ዩኒቨርሲቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የሰላም ግንባታ ሂደት አጠናከሮ ለማስቀጠል እና ለማገዝ በዩኒቨርሲቲው አከባቢ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ። በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ማዕከል በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የሐረማያ ወረዳ አመራሮች ፣ የወረዳው የጸጥታ ሀላፊዎች ፣ በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ የሚገኙ የቀበሌ አመራሮችና የሚሊሻ ሀላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል።

በመድረኩም ላይ የሐረማያ ዩኒቨርሲት የተማሪዎችና የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ጄይላን ወልይ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ፤ አከባቢው ሰላመዊ እና የተረጋጋ ከሆነ የዩኒቨርሲቲውም የሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ውጤታማ ስለሚሆን በመቀናጀት እና በመተባበር መስራት ይገባል ብለዋል። በመሆኑም ውጤታማ የሰላም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት እና ሀገራችን የጀመረችውን የሰላም ግንባታ ለማገዝ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንደሚሰሩ ጨምረው ጠቅሰዋል።

በመድረኩ የተገኙት የወረዳው አመራሮች እና የጸጥታ ሀላፊዎች ዩኒቨርሲቲው ይህንን መድረክ በማዘጋቱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ የአከባቢውን ሰላም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲወን የሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ለማገዝ በቅንጅት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

#ሐረማያዩኒቨርሲቲ