ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ 355 ተመራቂ ተማሪዎች የመስክ የቡድን ስልጠና /TTP / በሐረሪ ክልል በተመረጡ 9 ሳይቶች ላይ ለማህበረሰብ ሙያዊ ድጋፍና ህክምና አገልግሎቶችን መስጠት ላይ ይገኛሉ።

ተመራቂ ተማሪዎች እና ሱፐርቫይዘሮች በተመደብበት ሳይቶች  ”ደም በመለገስ የእናቶችን ሞት እንቀንስ” በሚል መሪ ቃል በስልጠና ሳይቶች ላይ የአካባቢውን ህብረተሰብ በማስተባበር በግንባር ቀደምትነት ደም ልገሳ እያካሄዱ ይገኛል በቀሪው የስልጠና ወቅት የደም ልገሳ ፕሮግራም በሁሉም ሳይቶች የአካባቢውን ማህበረሰብ እና የወረዳ አስተዳደር አካላትን ጭምር በማሳተፍ ደም ልገሳ ፕሮግራም እንደሚካሄድ ከኮሌጁ የህብረተሰብ አቀፍ የተግባር ስልጠና ማስተባበሪያ ቢሮ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል።

”ደም በመለገስ የእናቶችን ሞት እንቀንስ”