የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሰራተኞች ያካተተ ቡድን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኘ።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችና የጋዜጠኞች አባላትን ያካተተ ቡድን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኘ። ኮሚሽኑ #VisitOromia በሚል ንቅናቄ ኦሮሚያ ክልልን ተቀዳሚ የቱሪስ መዳረሻ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል። በተጨማሪም ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይም ውይይት ተካሂዷል። በተለይ ዩኒቨርሲቲው ምስራቅ ኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝና ወደፊትም እንደሚሰራ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕረዚዳንት ፕ/ር ጄይላን ወልዬ ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*