ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

 

Child Health and Mortality Prevention Surveillance (CHAMPS) የስራ መደቡ መጠሪያ: የመስክ ሰራተኛ   በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ለሚሠሩና መቀመጫቸውን በቀርሳና ወተር ኢትዮጵያ ላደረጉ የጥናትና ምርምር ፕሮጀክቶች የሙሉ ጊዜ የመስክ ሰራተኞችን ለመቅጠር ይፈልጋል:: የተቀጣሪዋ/ው የሥራ ድርሻ ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት ቤት ለቤት መስራት እንዲሁም በሙያ መርዳትና በመረጃ ማሰባሰብና በጤናው ዙሪያ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ማስተባበር ይሆናል::

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና ችሎታ

 • የትምህርት ዝግጅት
  • የመጀመሪያ ዲግሪ በሚድዋይፈሪ ነርስ/በሶሶሎጂ/አንትሮፖሎጂ እውቅና ካለው ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ የተመረቀ/ች ወይም
  • 10+3 ዲፕሎማ በሚድዋይፈሪ ነርስ/በሶሶሎጂ/አንትሮፖሎጂ እውቅና ካለው ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ የተመረቀ/ች እና የ3 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት
 • እጅግ በጣም ጥሩ የኦሮምኛ እና የአማርኛ የጽሁፍና የንግግር ችሎታ
 • በጣም ጥሩ የተግባቦት ችሎታ ያላት/ለው
 • ጥሩ የማደራጀትና የአመራር ችሎታ ያላት/ለው

የሚበረታታ

 • የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመግባባት ችሎታ
 • በጤና ተቋማትና ከህብረተሰቡ ውስጥ የቀደመ የሥራ ልምድ
 • መሠረታዊ የኮምፒውተር ችሎታ ማረጋገጫ

ብዛት             2

ቦታ                 ቀርሳ እና ወተር በሚገኙ ቀበሌዎች

ተጠሪነቷ/ ለሶሻል ሳይንስ ክፍል እና የህብረተሰብ ጥናት ክትትል ክፍል

ደሞዝ            በፕሮግራሙ የደሞዝ ደረጃ መሰረት ብር 8225 በወር

የመመዝገቢያ ቀን፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት

የመመዝገቢያ ቦታ፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረር ካምፓስ ቻምፕስ ፕሮጀክት ቢሮ

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

 የስራ ኃላፊነቶች

1.     ፕሮግራሙ በማሕበረሰቡ ውስጥ እየሰራ ያለውን ስራ ማሳለጥ

2.       የተለያዩ ስብሰባዎችን ማቀድ ማዘጋጀት መምራት

3.   የተሰሩ ስራዎች በጊዜውና በሁኔታ ሪፖርት ማድረግ

4.   የፕሮግራሙ አላማ አሰራር በተለያ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጥ

5.     የተለያዩ ቃለመጠይቆችን ውይይቶችን ከህብረተሰቡ ጋር ማድረግ

6.     የቤት ለቤት እንቅስቃሴ በማድረግ የእናቶች እና ሕፃናት ጤናን መደገፍ

7.     አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የቤት ለቤት እንቅስቃሴ በማድረግ መረጃ መሰብሰብ

8.    ከህብረተሰቡ መሪዎች፤ ከጤና የክስቴንሽን ሰራተኞች፤ ከሐይማኖት አባቶች፤ ከተለያዩ የህብረተሰብ አደረጃጀቶች ጋር በቅርበት መስራት

9.    ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት

 

No comments

Be the first one to leave a comment.

Post a Comment