HU Procurement, Finance and Property Administration Directorate

 

ፕሮኩዩርመንት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አመሠራረትና ታሪክ

የፕሮኩዩርመንት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሚል መጠሪያ ስም የተቋቋመው በአዲሱ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት በ2001 እ.አ.አ. ሲሆን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኮሌጁ ደረጃ ከነበረበት ከ2013 እ.ኤ.አ. ጀምሮ እቃ ግዥና ሽያጭ ዋና ክፍል፣ፋይናንስና በጀት መምሪያ እና ጠቅላላ አገልግሎት በሚባሉ መጠሪያዎች የሚታወቁ ሶስት የሥራ ክፍሎች እንደነበሩ ማስረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ዳይሬክቶሬቱ እነዚህን ሶስት የሥራ ክፍሎች በማቀፍ በአዲሱ አወቃቀር መሠረት የፕሮኩዩርመንት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተብሎ በዋናው ግቢ ወደ 83 የሚጠጉ ባለሞያዎች የሚኖሩት ሲሆን እነዚህም ባለሙያዎች በሶስት ንኡስ የሥራ ሂደቶችና በአንድ ዳይሬክፈቶሬት ሥር በመሆን ሥራቸውን ያከናውናሉ። ከዚህም በተጨማሪ በሐረርና ጭሮ ካምፓሶች በተባባሪ ዳይሬክቶሬት ደረጃ የተዋቀሩ በሐረር 46 ባለሙያዎች በጭሮ ደግሞ 23ባለሙያዎችን ይዞ ተደራጅቶ ይገኛል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ የተለያዩ ኮሌጆች የምርምር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና የአስተዳደር ዘርፍ ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛ ጊዜና በትክክለኛው ጥራት በመስጠት የውስጥና የውጪ ባለድርሻ አካላትን ለማርካት በመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል በሟሟላት የዩኒቨርሲቲውን ራእይ ለማሳካት ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር ጎን በመቆም የበኩሉን አስተዋጽዎ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

 1. ለዳይሬክቶሬቱ የባላንስድ ስኮር ካርድ አስፈላጊነት

አንድ ተቋም ስትራቴጂክ እቅዱን በባላንስድ ስኮር ካርድ በመቃኘት ከነደፈ በኃላ የተቋሙን ራእይ ለማሳካት ግቦቹን ከፋፍሎ በየደረጃው ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የሚደረስበትን ሁኔታ ካመቻቸ ተቋሙ በስትራቴኪክ እቅድ ጊዜ ውስጥ ሊደርስ ካሰበበት ቦታ ለመድረስና ራእዩን እውን ለማድረግ እንደሚችል በተለያዩ አገራት ውስጥ የሚገኙ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ መሆን ችለዋል፡፡በመሆኑም የባላንስድ ስኮር ካርድ ለፕሮኩዩርመንት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አስፈላጊነቱ ከዚህ እነደሚከተለው ተገልíል፡፡

 • የዳይሬክቶሬቱ ደንበኞች የሆኑትን የውስጥ ሰራተኞችንም ሆነ የውጪ ተገልጋዮችን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ የተቀመጡ ግቦችን ለማስፈፀም ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ያግዛል፡፡
 • በዳሬክቶሬቱ ውስጥም ሆነ በዩኒቨርሲቲው ከሚገኙ ሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በትብብር በመናበብና በቅንጅት እንዲሰራ ይረዳዋል፡፡
 • የተቋሙን ተልእኮ ለማሳካት ዳይሬክቶሬቱ ሊጫወት የሚገባውን ሚና በግልጽ ለይቶ ያሳውቃል፡፡
 • በዳሬክቶሬቱ ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር እንዲዘረጋና እያንዳንዱ ሰራተኛ በእኔነት ስሜት ስራውን በብቃት የሚያከናውንበት መልካም የስራ አካባቢ እንዲሆን የሚረዳው ሲሆን በአጠቃላይም የዳይሬክቶሬቱ ስራ በተቀመጠው አቅጣጫ ላይ ሆኖ በውጤት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን እገዛ ያደርጋል፡፡
 • በስትራቴጂክ እቅዱ ጊዜ ውስጥ የዳይሬክቶሬቱ ስራ በተቀመጠው መለኪያ አንጻር መከናወኑ የሚቃኝበትና የተመዛገበው ትክክለኛ ውጤት ሊሆን ከሚገባው ጋር በንጽጽር ታይቶ የሚለካበት ሲሆን በአጠቃላይ ዳይሬክቶሬቱ ለዩኒቨርሲቲው ራእይ መሳካት የሚጫወተው ሚና በግልጽ የሚታይበት ይሆናል፡፡
 • በዳሬክቶሬቱ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ሁሉ ብቃታቸውንና ችሎታቸውን አውቀው እንዲጠቀሙ ከማድረጉም በላይ ሁሉም በውጤታቸው የሚለኩበትና የተለያዩ ማበረታቻዎችን የሚያገኙበት እንዲሁም ጠንካራው ከደካማው የሚለይበት ስርአት እንዲዘረጋ ያደርጋል፡፡
 1. የዳይሬክቶሬቱ ራእይ

በከፍተኛ ደረጃ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እስከ 2015 እ.ኤ.አ. ድረስ ለትምህርትና ለስራ ተመራጭ ስፍራ እንዲሆን ማስቻል፡፡

 1. የዳሬክቶሬቱ ተልእኮ

በዩኒቨርሲቲው ራእይ በመንተራስ ወጥነት ያለው፣ጊዜን ያማከለ ደንበኛ ተኮር አገልግሎቶችን በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ፡፡

 1. የዳይሬክቶሬቱ ሞቶ

( We are committed to deliver quality service) /ጥራት ያለው አገልግሎት እንሰጣለን

 1. እሴቶች

የፕሮኩዩርመንት፣ ፋየናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እሴቶች ይኖሩታል፡፡

5.1.    ተጠያቂነት

 • ግልጽነትና ከሌሎች መማር መግባባትና እውቀትን ለሁሉም ማካፈል ፡፡
 • በተገቢው ጊዜ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት
 • የተመጣጠነ የሀብት ስርጭት እንዲኖር ማድረግ

5.2.    ተባብሮ መስራት

 • የመተጋገዝና እውቀትን በማጋራት አብሮ መስራት
 • ትብብርና አጋርነት፣ ለሌሎች የውጭና የውስጥ ተገልጋዮችና ደምበኞች ቅድሚያ መስጠት
 • አቅምን ባገናዘበ መልኩ አቅዶ መስራት

5.3.    አቅምን አሟጦ መጠቀም

 • የሙያ ብቃትን ማሳደግ
 • ውጤታማነት
 • ብቃት

5.4.    የአገልጋይነትን ስሜት ማሳደግ

 • ትሁትነት
 • ታማኝነት
 • ቁርጠኝነት
 • መልስ ሰጭነት፣ ለችግሮችና ለለውጥ ምላሽ መስጠት

5.5.    ከሌሎች ጋር ተባብሮ መስራት

 • በቡድን የመስራት መንፈስ
 • እየተማማሩ አብሮ መኖር
 • አሳታፊነት፣ሁሉም ሰራተኛ በውሳኔ ሰጭነት ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ
 1. የፕሮኩዩርመንት፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት SWOT ግምገማ

8.1.ጥንካሬ/ strength

 •  ዳይሬክቶሬቱ የሚከተሉት ጥንካሬዎች ይኖሩታል፡፡
 •  የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ መተግበርና አዲስ ሲስተምና አወቃቀር መፈጠር የተፈጠረው አወቃቀር ወይም ሲስተም የአሠራር ቅልጥፍናና ብቃትበአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ እንዲጎለብቱ ያደርጋል፡፡
 •  የአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋና የደንበኞችን እርካታ እንዲያሳድግ እንዲሆን
 • የተዘረጋ መሰረተ ልማት /Infrastructure / መኖር
 •  ለሠራተኛው /ባለሞያው የተሰጠው የመወሰን ስልጣንና አመኔታ