9ኛው የኢትዮጲያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሰሞኑን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለየዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡

 
በሸምሰዲን መሀመድ/ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

“በህገ መንግስታችን፣ የደመቀ ኢትዮጲያዊነታችን ለህዳሴአችን” በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሣምንት በተከበረው በዚህ በዓል ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉደዮችና ም/ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሣ በአሉን በምናከብርበት ጊዜ የኢትዮጲያ ህዝቦች፣ የተለየዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለየዩ ሃይማኖቶችና ቋንቋዎች እንደሁም የተለየዩ አኩሪ ባህሎችና ታሪኮች ያለን መሆኑን አውቀን እውቅናና ክብር በመሰጣጣት በአሉን በጋራ የምንዘክርበት ቀን ነው ብለዋል፡፡

nat nat2

ፕሮፌሰር ጨመዳ አያይዝውም እንደተናገሩት የዩኒቨርሲትው መምህራን፣ ሠራተኞችና ተማሪዎች ባአሉን ሲያከብሩ ብዙነታችን ውበታችን ብቻ ሣይሆን ውድ ሀብታችን ጭምር መሆኑን በመረዳት ከሁሉም በላይ በብዙ መስዋእትነት የተገኘው ህገ መንግስታችን የባአሉ መሠረት መሆኑን ተገንዝበው ሁላችንም በእኩልነት ለአገራችን ሠለምና እድገት በመነሣት በአገሪቱ በየዘርፉ እየተከናወነ ያለውን የህዳሴ ጉዞ ለማጎልበት የበኩላቸውን ለመወጣት ጠንክረው መሰራት እንደለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

pro chemedea

በበአሉ ላይ ተካፋይ የሆኑት አንደንድ መምህራኖችና ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በዓሉ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ መከበሩ በጣም እንዳስደሰታቸው ከመግለጣቸውም በተጨማሪ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ ትልቅ ፈይዳ እንደለው አመልክተዋል፡፡

   ከህዳር 20-26 ቀን 2007 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ በጽዳት ዘመቻ፣ በምርት ማሰብሰብ ሥራና በፓናል ውይይት ለአንድ ሳምንት የተከበረው ይሄው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአል የተጠናቀቀው በህገ-መንግስት ዙሪያ በተማዎች መካካልና በሠራተኛች መካከል በተደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር ነው፡፡ በውድድሩ ከ1ኛ-3ኛ ደረጃ ለወጡት አሸነፊዎች ከ3000 – 1000 ብር የሚደርስ ለኅዳሴው ግድብ የቦንድ ግዢ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

dcfgd fdgdgd

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.