ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት ቅጥር ለማካሄድ በተደረገው ውድድር ከፍተኛ ውጤት ያገኙ ሶስት ዕጩዎችን በህጉ መሰረት ለሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲው አስተዳድር ቦርድ ስምና ውጤታቸውን ባቀረበው መሰረት ከተወዳዳሪዎቹ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ ከታህሳስ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሹመቱን አፅድቆላቸዋል።

ዶክተር ጀማል ከመደበኛ የማስተማርና ምርምር ስራቸው ባሻገር ላለፉት ሶሥት ዓመታት የዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ከሥምንት ወራት በተጠባባቂ ፕሬዝዳንትነት ዩኒቨርሲቲያችንን በከፍተኛ ኃላፊነት አገልግለዋል።