የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድንች ዘር ማከማቻ መጋዘን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

 

4ሀረር መስከረም 20/2008 የአካባቢውን ህብረተሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማጎልበት የጀመረውን የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ በአንድ ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን ሶስት የድንች ዘር ማከማቻ መጋዘኖችን ለድንች ዘር አብቃይ አርሶ አደር ማህበራት አስረክቧል።
በኮምቦልቻ ወረዳ የመጋዘኑ ርክብክብ ትናንት በተከናወነበት ወቅት የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በተበታተነ ሁኔታ የሚያከናውነውን የማህበረሰብ አገልግሎት ለማጠናከር ባለፉት ሶስት ዓመታት የማህበረሰብ አገልግሎት ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል።የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግም በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን ከውጭ ዝርያዎች ጋር በማዳቀልና የበግ፣ፍየልና ዶሮ ጫጩቶችን ለአካባቢው አርሶ አደሮች ማሰራጨቱን ተናግረዋል።በወረዳው ቀቀሊ፣ቢሊሱማና ኤጉ ቀበሌ የተገነቡት የድንች ዘር ማከማቻ መጋዘኖች ዘር አቅራቢው አርሶ አደር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ባልተከተለ መንገድ ያከናውን የነበረውን የዘር አቀራረብ ስራ ችግር እንደሚያስወግድም አስታውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከተቀናጀ የዘር ልማትና ካስ ኬፕ ከተባሉ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ያስገነባቸው መጋዘኖች እያንዳንዳቸው እስከ 500 ኩንታል የድንች ዘር የመያዝ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱራዛቅ አህመድ በዞኑ በአመት 178 ሺህ ሄክታር መሬት በሁለት ዙር አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ በመስኖ እንደሚለማ ገልጸዋል።ከዞኑ ከ14 ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ አትክልት በአመት በማምረት አርሶ አደሩ እስከ ከሁለት ቢሊየን ብር የሚበልጥ ገቢ እያገኘ መሆኑን ጠቁመው የመጋዘኑ መገንባት የመስኖ ልማትን በማጎልበት የዘር አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።በወረዳው ኤጉ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አብደላ ሙሀመድ እንደተናገሩት የመጋዘኑ መገንባት አርሶ አደሩ በተበታተነ መንገድ የጀመረውን የዘር አቅርቦት በተቀናጀ ሁኔታ ለማከናወን ያግዛል።የቀቀሊ ገጠር ቀበሌ ነዋሪና አርሶ አደር ወይዘሮ አኒሳ አህመድ የመጋዘኑ መገንባት ምርጥ ዘር ፍለጋ ወደ ሌላ ቦታ የሚያደርጉትን ጉዞ በማስቀረት የነበረባቸውን አላስፈላጊ ወጪ እንደሚያስቀርላቸው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው ከማስተማርና ምርምር ስራው ጎን ለጎን የአካባቢውን ህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ለማጎልበት እያከናወነ ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር ንጉሴ ገልጸዋል።በጤና፣በትምህርት፣በነጻ የህግ አገልግሎትና ሌሎች ማህበረሰቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ በርካታ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው የሚያደርገውን የጤና አገልግሎት ስራ ለማጠናከር ባለፈው ዓመት 90 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒት ለሶስት ሆስፒታሎች እንደሰጠ መገለጹ ይታወሳል። 

3 comments on “የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድንች ዘር ማከማቻ መጋዘን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

 1. ayele ejere on said:

  I don’t know the Radio.

 2. ayele ejere on said:

  it is very good research center. Haramaya is a special university of agriculture sector. It produce many more important Researchers like Laureate Gabisa Ejeta, and others. I too a production of this fantastic beautiful University. so I’m very happy!

  • ayele ejere on said:

   It works on environmental protection education like Geography and environmental studies to help people to protect their environment by their self.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.