የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የውይይት መድርክ ተከፈተ

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተያዘ መርሀ – ግብር መሰረት ነባር ተማሪዎችን የሚያሳትፍ ለአራት ቀናት ከ20 – 25 / 2008 ዓ/ም የሚቆይ የውይይት መድርክ ተከፍቶ እየተካሄደ ይገኛል ፡፡

በውይይቱ ላይ ሀገራዊና ዩኒቨርሲቲውን የሚመለከቱ ጉዳዮች እንደሚነሱ የተገለጸ ሲሆን በዋነኛነትም የአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ፣ የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ይዘት ፣ የትምህርት ጥራትን የማስጠበቅ ስራና የባለድርሻዎች ሚና ፣ የዩኒቨርሲቲው የ2007 ዓ/ም እቅድ አፈጻጸምና የ2008 ዓ/ም እቅድ ይዘትን የሚመለከቱ ነጥቦች ቀርበው ከተማሪዎች ጋር ሰፊውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል ፡፡

በውይይቱ የመክፈቻ ስነስረአት ላይ ንግግር ያደረጉት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆኑት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ እንደገለጹት ስልጠናው ተማሪዎች  በአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ወቅት በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በትምህርትና በጤና አገልግሎት የነበሩ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችና ውስንነቶችን ለመገንዘብ እንዲችሉ እንደሚረዳና እንዲሁም  የሁለተኛውን እቅድ አገራዊ ተደራሽ ግቦችና የማስፈጸሚያ ስልቶችን በተለይም በትምህርቱ ዘርፍ ያለውን ለይተው በማወቅ ግበአት እንዲሰጡ ብሎም በትግበራው ላይ የላቀ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲችሉ የሚያዘጋጅ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

1

 

አክለውም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የትምህርት ጥራት በተለያዩ ምክንያቶች አሳሳቢ እየሆነ የመጣና በጋራ ሊሰራበት የሚገባ በመሆኑ እንዲህ ያሉ የጋራ የውይይት መድረኮች መካሄዳቸው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንቅፋት የሆኑ ምክንያቶችን ለመለየትና ችግሩንም ለመቅረፍ የተማሪው ፣ የመምህሩና የአመራሩ ሚና ምን እንደሆነ በግልጽ በማወቅ ተማሪው የትምህርት ጥራትን ለማጎልበት የድርሻውን መወጣት እንዲችል ትልቅ አስተዋጾ ያደርጋሉ ብለዋል ፡፡

በመሆኑም ተማሪው በአራቱ ቀናት የውይይት ጊዜ ውስጥ የሚቀርቡ ሪፖርቶችንና ሀሳቦችን አጽኖት ሰጥቶ በመከታተል በሰለጠነ ስርዓትና በነጻነት ሀሳቡን በመግለጽ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

2 3

 

በእለቱም የአንደኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡ ከቀናት በፊት ተመሳሰይ ውይይት ከዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች ጋር መደረጉ የሚታወስ ነው ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.