የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሄዱ

 

የህግ ተማሪዎች የምስለ ችሎት ውድድር የተለያዩ ህጎችን መሰረት በማድረግ የህግ ተማሪዎች የጹሁፍና የቃል ክርክር በማድረግ የሚወዳደሩበት ነው ፡፡ ውድድሩ በሀገር ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተማሪዎች መካከል ይካሄዳል ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚካሄዱ የምስለ ችሎት ውድድሮች መካከል የጄሳፕ ዓለም አቀፍ የህግ ተማሪዎች ውድድር በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው ፡፡ ሀገራችንን በመወከል በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በቅድሚያ በሀገር ደረጃ የሚደረገውን የማጣሪያ መወዳደር ማሸነፍ ይኖርባቸዋል ፡፡

ዘንድሮ ኢትዮጵያን በመወከል ዋሽንግተን ዲሲ በሚዘጋጀው የጄሳፕ ዓለም አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ የሚሳተፈውን ዩኒቨርሲቲ ለመለየት በመቀሌ በተካሄደ ውድድር የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቡድን

ተማሪ ተካልኝ ሸዊቶ ፣ ሮዛ ተስፋዬ ፣ ሙሐመድ ጀማል እና አ/ረዛቅ ረዳ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህግ ተማሪዎች ቡድንን በማሸነፍ ለውድድሩ ለማለፍ ችለዋል ፡፡

law

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ተማሪዎች ቡድን

በአሁኑ ወቅትም የህግ ተማሪዎቹ ቡድን ለውድድሩ የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አቅንቷል ፡፡ የቡዱኑ አባላት

በዩኒቨርሲቲው የህግ መምህርና የቡድኑ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ዳዊት ብርሀኑ እንደገለጹት የህግ ኮሌጁ በሂደት በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ እያሳደገ እንደመጣና በዚህም የሀገራችንን ብሎም የዩኒቨርሲቲውን ስም ለማስጠራት እንደቻለ አስታውሰው ዘንድሮም ኮሌጁ ሀገራችንን ወክሎ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ለመቅረብ ጠንክሮ በመስራት የሀገር ውስጡን የማጣሪያ ውድድር በበላይነት ለማሸነፍ ችለናል ብለዋል ፡፡ ዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው ውድድር ላይ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ዝግጋጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፡፡

ለ57ኛ ጊዜ ከመጋቢት18-28/2008ዓ.ም (March 27 – April 3, 2016) በሚዘጋጀው የጄሳፕ ዓለም ዓቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ከ90 ሀገራት የመጡ ከ 600 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.