የሀዘን መግለጫ

 

ሰሞኑን በሊቢያ እና በደቡብ አፍሪካ በንፁሀን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት አጥብቀው ያወግዙታል፡፡ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የሌሎች ሀገር ዜጎች ላይ በተካሄደው የዘረፋና ግድያ ጥቃቶች ንጹሀን ኢትዮጵያውያንም ተጠቂ በመሆናቸው መላውን የዩኒቨርሲቲያችንን ማህበረሰብ ያሳዘነና ወንድም ከሆነ አፍሪካዊ ሀገር ዜጋ የማይጠበቅ በመሆኑ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለኢትዮጵያውያኑና ለሌሎችም የጥቃቱ ተጋላጭ ለሆኑ አፍካዊያን አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድንም ሊቢያ በነበሩ ንጹሀን ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ አጥብቆ ያወግዘዋል፡፡ ይህ ድርጊት በሀገራችን ታሪክ ለበርካታ ዓመታት ጸንቶ የቆየውን የክርስትናና እስልምና እምነት ተከታዮችን ተቻችሎ የመኖር እሴት የማይሸረሸር እና አንድነታችንን አጠናክረን ድርጊቱን በማውገዝና በመከላከል አንድነታችንን ለአሸባሪዎች እንደምናሳይ የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ሙሉ እምነት አለው፡፡

በአጠቃላይ ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በአሸባሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ለተገደሉ ዜጎቻችን ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ መጽናናትን ይመኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችንም አሸባሪነትንም በፅኑ የሚያወግዝ ሲሆን ሀገራችን የጀመረችውን የጸረ ሽብር ትግልም አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.