የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፤ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም አሁን የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ የአለምአቀፉን የማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ማህበር 2016 ኖርማን ቦርላግሽልማትአሸናፊሆኑ

 

ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ ላለፉት ሶስት አስር ዓመታት በአፍሪካ የአፈር ለምነትን ለማሻሻል ላደረጉት ቁርጠኛ አስተዎፆኦም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የአፈር ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ ለሽልማት የበቁት የአፈር ለምነትን በማሻሻልና የተፈጥሮ ሃብት በመጠበቅ ከ11 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ የእርሻ መሬት ያላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደርግ የላቀ አስተዎጽኦ በማከናወናቸው ነው።

የአፈር መከላትና መሸርሸር፣የአፈር አሲዳማነት ባህሪን እና አልሚነት እጥረት ችግር ለመቅረፍም ፕሮፌሰሩ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ የ2014ቱን የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ሽልማት አሸናፊ ነበሩ፡፡የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት ለፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢጣልያ ሮም ከተማ የዓለም አቀፍ የዓመቱ አምባሳደርነትን ሹመት ተቀብለዋል ሲል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

ፕሮፌሰር ተካልኝ ማሞ የ2007 ዓ.ም የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ መፅሄት ልዩ እንግዳ የነበሩ ሲሆን ዝርዝር ስራዎቻቸውን ያስነበበችውን መፅሄት ላላገኛችሁ በፒዲኤፍ እናቀርብላችኋለን፡፡

Prof-Teka

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.