ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከህንድ አገር ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከድሬደዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪና ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ከምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ለመጡ 300 የአካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ እግር ገጠማ አገልግሎት ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዚህ አገልግሎት በርካታ አቅመ ደካማ የሆኑና አገልግሎቱን ለማግኘት የማይችሉ አረጋውያን ፣ ህጻናትና ሴቶች የሰው ሰራሽ እግር ገጠማው እየተካሄደላቸው ይገኛል ፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሐረር ጤና ሳይንስ ጊቢ ውሰጥ ለተከታታይ 25 ቀናት የሚሰጠውን ይህን አገልግሎት ለማግኘት የመጡ ተገልጋዮችም ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀላቸው ማረፊያ ውስጥ ሆነው አገልግሎቱን እያገኙ ነው፡፡