አስደሳች ዜና ለትምህርት ፈላጊዎች

 

አንጋፋው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት በአዲስ መልክ በሰው ሐይልና በቁሳቁስ ራሱን አደራጅቶ ለ2008 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን በሩን ለትምህርት ፈላጊዎች ክፍት አድርጓል፡፡

ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ትምህርት ሚኒስቴር ለ2008 ዓመተ ምህረት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያወጣውን መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎችን በአዳዲስና በነባር የትምህርት ዘርፎች እና ካንፓሶች አመላካቾችን ተቀብሎ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ስለሆነም በተከታታይና በርቀት ትምህርት መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች ከነሐሴ 20/2007 ዓመተ ምህረት እስከ መስከረም 20/2008 ዓመተ ምህረት ድረስ በመርሃ- ግብሩ ማዕከላት በሐረር ሐረር ጤናና ህክምና ሳይንስ፣በጭሮ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጭሮ ካምፓስ፣ በጨለንቆ መታ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት፣ በድሬደዋ ድሬደዋ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት፣ በጅግጅጋ ጅግጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በሐረማያ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በደስታ እየገለጸ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች ማመልከት የሚቻል መሆኑን በድጋሚ እንገልፃለን፡፡

በመጀመሪያ ዲግሪ

 • በሒሳብ አያያዝና ፋይናንስ (Accounting & Finance)
 • በሥራ አመራር (Management)
 • በሕዝብ አስተዳደር (Public Administration)
 • በሶሲዮሎጂ (Sociology)
 • በክሊኒካል ነርሲንግ (Clinical Nursing)
 • በፋርማሲ (Pharmacy)
 • በኤሌክትሪካል ምህንድስና (Electrical Engineering)
 • በሲቪል ምህንድስና (Civil & Urban Engineering)
 • በሕግ (Law)
 • በሳይኮሎጂ (Psychology)
 • በጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን (Journalism and Communication)
 • በኮምፕዩተር ሳይንስ (Computer Science)
 • በምጣኔ ሀብት  (Economics)
 • በገጠር ልማትና ግብርና ኤክስቴንሽን (RDAE)
 • ሶፍትዌር ኢንጂነርንግ
 • አፋን ኦሮሞ፤ሥነ ጽሑፍና ኮሚኒኬሽን (Afan Oromo, Literature & Communication)
 • በአግሪካልቸራር ኢኮኖሚክስና አግሪ ቢዝነስ አመራር (Agri.Economics & Agribusiness Management)
 • በተፈጥሮሐብት አስተዳደር(Natural resource Management)
 • በዕፅዋት አበቃቀል ጥናት (Horticulture)
 • Geographic Information System (GIS)
 • Urban planning
 • Tourism Development and Hotel Management
 • በስነ-ትምህርት (Teachers Education ) እንዲሁም
 • በልዩ ሙያዊ ስልጠና “CISCO` Academy:-  IT Essential (A+ Standard),  CCNA Rooting & Switching and CCNA Security

በሁለተኛ ዲግሪ

 • ግብርና ኮሙኒኬሽን እና ኢኖቬሽን ልማት (Agricultural Communication & Innovation Development, MSc)
 • ግብርና ምጣኔ (Agricultural Economics, MSc)
 • ግብርና ምጣኔ እና ገጠር ልማት (Agricultural Economics and Rural Development, MSc)
 • የትምህርት ሥራ አመራር (Educational Leadership, MA)
 • ሶሾሎጂ (Sociology, MA)
 • የልዩ ፍላጎትና የአካቶ ትምህርት (Special Needs & Inclusive Education, MA)
 • ሶሻል ሳይኮሎጂ (Social Psychology, MA)
 • አፋን ኦሮሞ ቲቺንግ (Afan Oromo Teaching, M.A)
 • አፋን ኦሮሞ አፕላይድ ሊንጉስቲክ (Afan Oromo Applied Linguistics, M.A.)
 • አፋን ኦሮሞ  ስነሥሑፍ (Afan Oromo Literature, M.A.)

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት

ለተጫማሪ መረጃ፡- +251 255530057 /+251 255530020

+251 255530372 /+251 255530315 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

Web Site: Www.haramaya.edu.et/Directorate of Continuing & Distance Education

One comment on “አስደሳች ዜና ለትምህርት ፈላጊዎች

 1. salmn debew on said:

  dear sir
  i would like to follow education from haramaya university through distance programme from adiss ababa . i need your advice to start and registere on the program soon.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.