አስደሳች ዜና ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ያልሆነው የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ለ2011 ትምህርት ዘመን በነባር የተከታታይ ትምህርት ዘርፎች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በድህረ-ምረቃ ተከታታይ ፕሮግራም (ቅዳሜና እሁድ) ማስተማር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም አመልካች ከነሐሴ 29/2010 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ ብር 50 (አምሳ) በመክፈል፤ ቅጹን በመሙላትና የመጀመሪያ ድግሪ ትምህርትና ሌሎች ማስረጃዎችን በማያያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ማቅረብ ይቻላል:: የምዕራብ ሐረርጌ ዞን አመልካቾች ማመልከቻቸውን በጭሮ ከተማ ለሚገኘው ኦዳቦልቱም ዩኒቨርሲቲ ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ (ለአቶ ልደቱ ኃይሌ) መስጠት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን::

የመመዝገቢያ ጊዜ፡: ከነሐሴ 30/2010 እስከ መስከረም 18/2011 ዓ/ም

የፈተና ቀን፡    መስከረም 24/2011

የፈተና ቦታ፡  ዋናው ግቢ፤ ሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ጭሮ ኦዳቦልቱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ

የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው::

  1. የትምህርት ሥራ አመራርና አስተዳደር (Educational Leadership and Management, M.A.) በሐረማያ ዋና ግቢ፤ ሐረርና ጭሮ
  2. ሰላም እና ልማት ጥናት (Peace and Development Studies, M.A.) በሐረማያ ዋና ግቢ፤ ሐረርና ጭሮ
  3. ሶሻል ሳይኮሎጂ (Social Psychology, MA) በሐረማያ ዋና ግቢ፤ ሐረርና ጭሮ
  4. አየር ለውጥና የአደጋ ሥራ አመራር (Climate Change & Disaster Risk Management, M.A.) በሐረማያ ዋና ግቢና ጭሮ
  5. ግብርና ኢኮኖሚክስ (Agricultural Economics, M.Sc.) በሐረማያ ዋና ግቢ፤ሐረርና ጭሮ
  6. ቢዝነስ አስተዳደር (Business Administration, M.B.A.) በሐረር ካምፓስ ብቻ

 የመመዝገቢያ ቅጽና ዝርዝር መረጃ: ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ወይም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ገጽ www.haramaya.edu.et. ይገኛል::

የክፍያ መጠን፡

በዋናው ግቢ ሐረርና ጭሮ ብር 700 በአንድ ክሬዲት (credit hour) እና 10% የአገልግሎት ክፍያ፤ ለ30 ክሬዲት ለኮርስ፡ ለሱፐርቪዥና ቴሲስ ፈተና ብር 32,100.00 ((ሰላሳ ሁለት ሺ አንድ መቶ)፡፡በቢዝነስ አስተዳደር ፕሮግራም ተጨማሪ በየተረሙ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ይከፈላል፡፡

Click  To Get Application form for Master CEP-2011 EC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.