አስደሳች ዜና ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

 

ድህረምረቃፕሮግራምዳይሬክቶሬት

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ያልሆነው የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ለ2010 ትምህርት ዘመን በነባርና አዲስ የተከታታይ ትምህርት ዘርፎች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በድህረ-ምረቃ ተከታታይ ፕሮግራም (ቅዳሜና እሁድ) ማስተማር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም አመልካች ከነሐሴ 29/2009 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ ብር 50 (አምሳ) በመክፈል፤ ቅጹን በመሙላትና የመጀመሪያ ድግሪ ትምህርትና ሌሎች ማስረጃዎችን በማያያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ማቅረብ ይቻላል:: የምዕራብ ሐረርጌ አመልካቾች ማመልከቻችሁን በጭሮ ከተማ ለሚገኘው ኦዳቦልቶም ዩኒቨርሲቲ ለሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይ ትምህርት አስተባባሪ መስጠት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን::

የመመዝገቢያ ጊዜ፡: ከነሐሴ 29/2009 እስከ መስከረም 15/2010 ዓ/ም

የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው::
1. የትምህርት ሥራ አመራርና አስተዳደር (Educational Leadership and Management, MA)
2. ሶሾሎጂ (Sociology, MA)
3. ሰላም እና ልማት ጥናት (Peace and Development Studies, M.A.)
4. ሶሻል ሳይኮሎጂ (Social Psychology, MA)
5. ሥርዓተ-ጾታ እና ልማት ጥናት (Gender & Development Studies, M.A.)
6. Climate Change & Disaster Risk Management (M.A.)
7. Geography and Environmental Studies (Specialization in Environment & Land Resource Management; Specialization in Urban and Regional Development Planning(M.A.)
8. አፋን ኦሮሞ ሊንጉስቲክ (Afan Oromo Linguistics, M.A.)
9. ኦሮሞኛ ስነሥሑፍ (Afan Oromo Literature, M.A.)
10. አፋን ኦሮሞ ቲቺንግ (Afan Oromo and Literature Teaching, M.A)

የመመዝገቢያ ቅጽና ዝርዝር መረጃ: ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 ወይም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ገጽ www.haramaya.edu.et. ይገኛል::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.