አስደሳች ዜና ለመደበኛ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፣

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት በዋናው ግቢና በሐረር ካምፓስ  በልዩ ልዩ የሦስተኛና ሁለተኛ ዲግሪ መርሃ-ግብሮች ትምህርት ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን በደስታ ይገልፃል።

 በ2008 የትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ዲግሪ አዲስ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ነሐሴ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል፡፡ ፈተናው በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ዋናው ቅጥር ግቢ እና ለጤና ሳይንስ የትምህርት ፕሮግራሞች በሐረር ጤና እና ሜዲካል ሳይንስ ሐረር ካምፓስ ይሰጣል፡፡ ለሦስተኛ ዲግሪ አዲስ አመልካቾች የመጨረሻ የማመልከቻ ቀን ነሐሴ 25/ 2007 ነው፡፡

አመልካቾች በዩኒቨርስቲው በመሰጠት ላይ ያሉትን የትምህርት ፕሮግራሞች በዩኒቨርስቲው ድህረ-ገፅ http://www.haramaya.edu.et ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0255530020 እና 0255530332 ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይቻላል፡፡

New Programs to be Launched in 2015/16 Academic Year 

  1. PhD in Teaching English as a Foreign Language
  2. PhD in Peace and Development Studies
  3. PhD in Medical Microbiology
  4. PhD in Education with Streams (Curriculum Studies, Educational Leadership and Policy Studies, Educational Psychology, and Inclusive Education)
  5. MSc in Maternity and Neonatal Nursing
  6. MSc in Agricultural and Applied Economics
  7. MA in Peace and Development Studies
  8. MA in Climate Change and Disaster Risk Management (CCDM)
  9. MA in Adult Education and Lifelong Learning

  Sincerely,

 Mengistu Urge (PhD)

Director, Postgraduate Program Directorate

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.