ማስታወቂያ

 

ለዩኒቨርሲቲው እና ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የክረምት ትምህርት ፕሮግራም የነፃ ትምህርት ዕድል ፈላጊዎች በሙሉ

ዩኒቨርሲቲያችን በ2010 በተከታታይ፤ በርቀትና በክረምት ትምህርት ፕሮግራሞች ለዩኒቨርሲቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የነፃ ትምህርት እድል ለመስጠት ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ባፀደቀው ደንብና መመሪያ መሰረት የተዘጋጀዉን መስፈርት አሟልተዉ በመወዳደር ለሚመረጡ ብቁ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች የነፃ ትምህርት እድል እየሠጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት እያንዳንዱ አመልካች (ተወዳደሪ) ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ የተዘረዘሩትን የነፃ ትምህርት ዕድል መወዳደሪያ መስፈርቶችን ማሟላታችሁን በማረጋገጥ፤ አስፈላጊ የትምህርት የሥራና ተያያዥ ኦሪጅናል መረጃዎች እና የማይመለሱ ኮፒዎችን በመያዝ በተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በግንባር  በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ብቻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከነዚህ ቀናት ዉጭ ማንኛዉንም ጥያቄዎች የማንቀበል መሆናችን እንገልጻለን፡፡

ሀ. ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ የነጻ ትምህርት ዕድል መስፈርቶች

 1. ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ዩኒቨርሲቲውን ያገለገለ/ያገለገለች፤
 2. ሕጋዊ የሆነ የጋብቻ ሰነድ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤(ለትዳር ባልደረባ ለሚጠይቁ)
 3. የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤት የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 4. ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የዲሲፕሊን እርምጃ ያልተወሰደበት/ያልተወሰደባት፤
 5. በዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቅሞ የማያውቅ/የማታውቅ እና
 6. ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚው/ተጠቃሚዋ የትዳር ባልደረባ ትምህርቱን/ቷን እስኪጨርስ/እስክትጨርስ ድረስ ነጻ የትምህርት ዕድሉን ያስገኘ/ች የትደር ባልደረባ ዩኒቨርሲቲውን ያለማቋረጥ ለማገልገል ህጋዊ የውል ስምምነት መፈረም፡፡

 ማሳሰቢያ፡ በሚያመለክቱት የትምህርት መስክና ፕሮግራም የትምህርት መስኩ መኖሩንና መግቢያ መስፈርቶቹን ማሟላታችሁን መረጋገጥ ግዴታ አለባችሁ፡፡ የአካባቢዉ ማህበረሰብ አመልካቾች ከቀበሌ፤ ከወረዳና ከዞን መስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤና መረጃዎች መያያዝ ያስፈልጋል፡፡

 ለ. ለድህረ-ምረቃ (ሁለተኛ ዲግሪ) የሚሰጥ የነፃ ትምህርት ዕድል መስፈርቶች

 1. አራት ዓመትና ከዚያ በላይ ዩኒቨርሲቲውን ያገለገለ/ያገለገለችና ቋሚ ሠራተኛ የሆነ/ች፤
 2. የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤት የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 3. ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የዲሲፕሊን እርምጃ ያልተወሰደበት/ያልተወሰደባት፤
 4. የነጻ ትምህርት ዕድል የተጠየቀበት የትምህርት መስክ ለዩኒቨርሲቲው በተለይ ደግሞ ለትምህርት/ለሥራ ክፍሉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለመኖሩ አሳማኝ መረጃ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 5. በማንኛውም የትምህርት መስክ ሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪ የሌለው/ላት፤
 6. የነፃ ትምህርቱን ተምሮ/ራ ከጨረሰ/ች በኋላ ዩኒቨርሲቲውን ቢያንስ ለአራት ዓመት ለማገልገል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ሕጋዊ ስምምነት ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ/ች፡፡

ማሳሰቢያ፡ በሚያመለክቱት የትምህርት መስክና መደበኛ ያልሆኑ የድህረምረቃ ፕሮግራም የትምህርት መስኩ መኖሩን፤ መግቢያ መስፈርቶቹን ማሟላታችሁንና የመግቢያ ፈተና ማለፍችሁን መረጋገጥ ግዴታ አለባችሁ፡፡ የአካባቢዉ ማህበረሰብ አመልካቾች ከቀበሌ፤ ከወረዳና ከዞን መስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤና መረጃዎች መያያዝ ያስፈልጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.