ማስታወቂያ የነፃ ትምህርት ዕድል መወዳደር ለምትፍልጉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ!!!!!

 

ዩኒቨርሲቲያችን በተከታታይ፣ በርቀትና በክረምት ትምህርት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና አካባቢው የነፃ ትምህርት እድል ለመስጠት ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም ባፀደቀው ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በክረምት ትምህርት መርሃ-ግብር የነፃ ትምህርት እድል ለመወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

እያንዳንዱ አመልካች (ተወዳደሪ) ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ    የተዘረዘሩትን የነፃ ትምህርት ዕድል መስፈርቶችን በማሟላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን መረጃዎችና ማስረጃዎች በማቅረብ  በተከታታይና ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በግንባር  በመቅረብ  በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ሀ. ለመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ የነጻ ትምህርት ዕድል መስፈርቶች

 1. ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ዩኒቨርሲቲውን ያገለገለ/ያገለገለች፤
 2. ሕጋዊ የሆነ የጋብቻ ሰነድ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤(ለትዳር ባልደረባ ለሚጠይቁ)
 3. የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤት የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 4. ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የዲሲፕሊን እርምጃ ያልተወሰደበት/ያልተወሰደባት፤
 5. በዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቅሞ የማያውቅ/የማታውቅ እና
 6. ነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚው/ተጠቃሚዋ የትዳር ባልደረባ ትምህርቱን/ቷን እስኪጨርስ/እስክትጨርስ ድረስ ነጻ የትምህርት ዕድሉን ያስገኘ/ች የትደር ባልደረባ ዩኒቨርሲቲውን ያለማቋረጥ ለማገልገል ህጋዊ የውል ስምምነት መፈረም፡፡

ለ. ለድህረ-ምረቃ (ሁለተኛ ዲግሪ) የሚሰጥ የነፃ ትምህርት ዕድል መስፈርቶች

 1. አራት ዓመትና ከዚያ በላይ ዩኒቨርሲቲውን ያገለገለ/ያገለገለችና ቋሚ ሠራተኛ የሆነ/ች፤
 2. የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ውጤት የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 3. ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የዲሲፕሊን ኮሚቴ የዲሲፕሊን እርምጃ ያልተወሰደበት/ያልተወሰደባት፤
 4. የነጻ ትምህርት ዕድል የተጠየቀበት የትምህርት መስክ ለዩኒቨርሲቲው በተለይ ደግሞ ለትምህርት/ለሥራ ክፍሉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለመኖሩ አሳማኝ መረጃ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
 5. በማንኛውም የትምህርት መስክ ሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪ የሌለው/ላት፤
 6. የነፃ ትምህርቱን ተምሮ/ራ ከጨረሰ/ች በኋላ ዩኒቨርሲቲውን ቢያንስ ለአራት ዓመት ለማገልገል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ሕጋዊ ስምምነት ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ/ች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.