ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ2011 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!

 

የ2011 የትምህርት ዘመንን ያለምንም ችግር ለማካሄድ እንዲያሥችል ታሥቦ ከአገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ መምህራንና የአሥተዳደር ሠራተኞች ፣ ከፌደራልና ክልል የፀጥታ አካላት ፣ ከአካባቢያችን ማህበረሰብና የአሥተዳደር አካላት ጋር ሲካሄድ የነበረው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቆ የእናንተን የተማሪዎቻችንን መምጣት በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።

ቀሪው የውድ ተማሪዎቻችን መምጣትና በአዲስ መንፈስ የመማር ማስተማር ሂደትንት በማከናወን ሰላማዊ የትምህርት ዘመንን ማሳለፍ ይሆናል።

የምዝገባ ቀናቱን ለማስታወስ!!

– የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 13-15
– የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 17-19/2011 ዓ.ም ይካሄዳል

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ሥልክ 025 553 0355

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.