ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ

 

የምዝገባ ቀን ለውጥ ተደርጓል!

የ2012 የትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀንን አስመልክቶ መስከረም 5 ቀን ባወጣነው ማስታወቂያ ምዝገባ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ከመስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት እንደምትችሉ አሳውቀን ነበር፡፡

ሆኖም የዝግጅት ስራዎችን ለማጠናቀቅ ሲባል ነባር ተማሪዎች ከመስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን እንድትገቡና ምዝገባም መስከረም 28 እና 29 ተከናውኖ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀመርና ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርት በሚጀመርበት መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አዲስ የሚመደቡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ከጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን እንዲገቡና ጥቅምት 3 ገለፃ ተደርጎላቸው ጥቅምት 04 እና 05/2012 ዓ.ም ምዝገባ አካሂደው ጥቅምት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግቢ ገብተው ምዝገባ መስከረም 11-12/2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡- 025 553 0355

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.