ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

 

የፊታችን ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ
በአንድ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከፍተኛ
ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ማህበረሰብ በሙሉ በዚህ ሀገራዊ ጥሪ የበኩሉን ድርሻ
ለመወጣት እንድችል በተጠቀሰው እለት ማለትም ሰኞ ሐምሌ
22 ቀን 2011 ዓ/ም ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት (2፡00) ላይ
በፓርኪንግ ሎት በመሰባሰብና ለችግኝ መትከያ ወደተዘጋጁት
ቦታዎች በመሄድ በችግኝ ተከላ ስራው ላይ በመገኘት ሀገራዊ
የዜግነት ግዴታችሁን በመወጣት ለተተኪው ትውልድ
የሚተርፍ አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.