ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ግልጽና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን አዲስ የፈርማሲ አገልግሎት አሰጣጥ ጀመረ፡፡

 

ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ በሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ውስጥ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፍነበት የፈርማሲ አገልግሎት ለመስጠት እንዲይሰችል የዘረጋወ አዲስ አሰራር ጥቅምት 4/2008 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል ፡፡

1

አዲሱ አሰራር እንደሌሎቹ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች ሀገር በቀል የሆነና በሐገር ደረጃ በስፋት በመተግበር ላይ የሚገኝ አሰራር እንደሆነና ተግባራዊ በሆነባቸው ሆስፒታሎች ውስጥም ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ የሚገኝ አሰራር እንደሆነ ተገልጾል ፡፡

አገልግሎቱን በህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልለመጀመር እንዲቻል የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ለአስራ ሁለት ቀናት ሀምሳ ስድስት ለሚሆኑ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቶል፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ የአስተዳደርና ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱል ባሲጥ ሙሳ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ ለህሙማን እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማሻሻልና በምስራቁ የሐገራችን ክፍል ተመራጭ ሆስፒታል ለማድረግ የሆስፒታሉ ቦርድ ፣ ሰራተኞችና ዩኒቨርሲቲው በመንግስት አቅታጫ መሰረት ጠንክረው እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡

2

በተለይም ሆስፒታሉን ጽዱና ምቹ በማድረግ የመድሀኒት አቅርቦትን በማሻሻል የህሙማንን እርካታ ለመጨመር እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው በዕለቱም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው አዲስ የፋርማሲ አገልግሎት አሰጣጥ የዚሁ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

3

የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚንሰተር የህከምና አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብረሀም እንዳሻው  በምርቃት ስነስርአቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት መንግስት ሆስፒታሎች ላይ ተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚያቀርበውን ቅሬታ በመቀበል የሆስፒታሎችን አገልግሎት አሰጣጥ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለማሻሻል ካለፈው አምስት አመት ጀምሮ ሀገር አቀፍ የሆስፒታሎች መመሪያ በማውጣት በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታወሰው በዚህ መሰረትም ሂወት ፋና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የጀመረው አዲስ አሰራር ሆስፒታሉ የሚሰጠውን የአግልግሎት ጥራት አንድ እርምጃ ወደፊት ሊያሸጋግረው የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕ/ት ፕ/ፌ ጨመዳ ፊኔንሳ በበኩላቸው የህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የሚገኝ ብቸኛው የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መሆኑን ገልጽወ ዩኒቨርሲቲውም ሆስፒታሉን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

4

በተለይም ደግሞ የፋርማሲ አገልግሎትን ለማሻሻል ከተደረጉ ጥረቶች መካከል አዲስ የፈርማሲ እስቶርና የፋርማሲ ዲስፔንሰሪ ማስገንባት  ፣ BPRን ተግባራዊ ማድረግና የሰራተኛ ቁጥርን በሚፈለገውና ገበያው በፈቀደው መሰረት መጨመር የሚጠቀሱ እንደሆኑ ገልጸው አዲሱ የፈርማሲ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በሚገባ ተግባራዊ ሆና የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር እንዲያስችል መላው የሆስፒታሉ ሰራተኛ ያላለሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባው አመልክተዋል ፡፡

5

አዲሱ አሰራር መተግበሩ ተገልጋዮች የታዘዘላቸውን መድሀኒት ለመግዛት ሂሳብ ለመክፈልና መድሀኒቱን ለመውሰድ የተለያዩ ክፍሎች እዲሄዱ የሚስገድደውን አሰራር ያስቀረና ክፍያና መድሀኒት እንዲሁም የመድሀኒት አጠቃቀምን በተመለከተ በአንድ ቦታ በተለያዩ ባለሞያዎች በተቀላጠፈ መለኩ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ማስቻሉ ተነግሯል ፡፡ በተጨማሪም አዲሱ አሰራር ከዚህ ቀደም በፋርማሲዎችና  በስቶሮች መካከል በነበረ አለመናበብ ይፈጠሩ የነበሩ የመድሀኒት እጥረቶችን በማስወገድ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር ያሰፈነ እንደሆነም ነው የተገለጸው ፡፡

6

በዕለቱ ከጤና ጥበቃ ሚኒስተር የተገኙ እንግዶች ፣ የሆስፒታሉ ቦርድ አባላትና  የዩኒቨርሲቲው ሀላፊዎች  አዲሱን የፋርማሲ አገልግሎት ለመስጠት የተገነባወን ህንጻ መርቀው በመክፈት የአገልገሎቱን አሰጣጥ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ፡፡                       

Leave a Reply

Your email address will not be published.

HTML tags are not allowed.